fbpx

የግዕዝ አኀዞች ከየት መጡ?

የግዕዝ አኀዞች አሁን ላይ በአብዛኛው ወይም ሙሉ ለሙሉ ማለት ይቻላል በጥቅም ላይ ባይውሉም...

የግዕዝ አኀዞች

የግዕዝ አኀዞች አሁን ላይ በአብዛኛው ወይም ሙሉ ለሙሉ ማለት ይቻላል በጥቅም ላይ ባይውሉም በሃይማኖት መጻሕፍት እና ቀደም ባሉ ጊዜያት በተጻፉ መጻሕፍቶች ላይ ተጽፈው እናያለን። የዓረብ ቁጥሮች እየተለመዱ በመሄዳቸው የግዕዝ አኀዞች እየተረሱ መተዋል። ለዚህም እነደምክንያትነት የሚጠቀሰው ለቁጥር ማስላት ስራ(calculation) ቅልጥፍና አለመመቸታቸው፣ ከአኀዞቹ ውስጥ ዜሮ አለመኖሩ ( ይሁንና አንዳንድ ምሁራንም ይህን በማጤን ዜሮን ለማበጀት መሞከራቸውን ተመልክተናል ፊደል “የ” አልቦ ወይም ዜሮን “0” እንዲተካ በማለት) ፣ በትምህርትና በዕለት ከዕለት ስራችን ውስጥ በስፋት አለመጠቀማችን አኀዞቹን ዛሬ ድረስ እንዳንጠቀማቸው ሆኗል።

የግዕዝ አኀዞች ከየት መጡ?


የግዕዝ አኅዞች በአብዛኛው ከጽርዕ (ግሪክ) ፊደላት የተወረሱ ናቸው። ( የግሪክ ፊደላትና የግዕዝ አኀዞች የሚለውን ልጥፍ ይመልከቱ)። ሆኖም ግን ግዕዝ ከራሱ ግዕዝ ፊደላት አንዳንዶቹን ወስደው ከራስጌና ከግርጌ ሰረዝ በመጨመር ወደ አኀዝነት ለውጠዋቸዋል። ለምሳሌ ያየን እንደሆነ ከታች ያለውን ምስል ይመልከቱ።

የአኀዞቹ ቅርፅ ከላይ ያሉትን ስንመለት አሐዙና ፊደሉ መለያ እንዲኖረው ለማድረግ በአኀዙ ላይና ታች ሠረዝ እንዲኖረው ተደርጓል። እንዲሁም የግዕዝ አኀዞች ስያሜ ከዓረብ ቁጥሮች ጋር እጅጉን ተመሣሣይነት አለው፡፡ የአኀዞቹን መልክና ስያሜ በፊደልና በአኀዝ ከዓረብ ቁጥሮች ጋር በማስተያየት ከዚህ ግርጌ ቀርቧል፦

እዚህ ልጥፍ ላይ የሚጨምሩት ይዘት አለ? ወይስ የሚያበረክቱት አዲስ ልጥፍ አለ? እንግዲያውስ ይህንን ይጫኑ

One Response

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

የቴሌግራም ቤተሰብ ይሁኑን
በኢንስታግራም ይከተሉን
የፌስቡክ ገጻችንን ይወዳጁ
ምርጥ የተሸጡ ምርቶች

በማህበራዊ ሚዲያ ያጋሩን

በመረጡት ሚዲያ በማጋራት እንደርስዎ ሌሎችም እንዲያቁን ያድርጉ።

Share on facebook
ፌስቡክ
Share on twitter
ትዊተር
Share on telegram
ቴሌግራም
Share on pinterest
ፒንትረስት

በማህበራዊ ሚዲያ ይከተሉን

© ፳፻፲፪ geezfonts.com