fbpx

የሳምንቱ ፊደል- ፊደል -‘ሀ’

ሀሌታው ሀ በአማርኛ የፊደል ገበታ መጀመሪያው ላይ የሚገኝ ፊደል( ግዕዙ ሆሄ) ነው። ሀ- ከቀድሞው የፊደል ገበታ

ሀሌታው ‘ሀ’

ሀሌታው ሀ በአማርኛ የፊደል ገበታ መጀመሪያው ላይ የሚገኝ ፊደል( ግዕዙ ሆሄ) ነው።
ሀ- ከቀድሞው የፊደል ገበታ አደራደር ማለትም (አበገደ…) ወደ (ሀለሐመ…) ሲቀየር የፊደል መጀመሪያ ከ አልፋው “አ” ወደ ሀሌታው “ሀ” ተቀይሯል። አልፋው አ አልፋው አ ተለውጦ ሀሌታው(ሆይ) ሀ መጀመሪያ የሆነበት ምክንያት አንዳንድ ምሁራን እንደሚአስረዱት ሕፃናትን በማስተማር ጊዜ አ በሉ ከማለት ይልቅ ሀ በሉ ማለት ከውስጥ ያለውን የእስትንፋስ ኃይል ወደ ውጭ የሚስብ ስለሆነ ሆይ ሀ የመጀመሪያ ፊደል እንዲሆን በምስጢር አመዛዝነውታል ይባላል ። እስትንፋስ የሌለውን ፊደል አ መጀመሪያ ከማድረግና አ ከማለት በፊት የእስትንፋስ ድምጽ መስጠት ይቀድማል ብለው ሀ አሉ። ልብ አድርግ የሀን መልክ ስታየው የተከፈተ አፍ መስሎ ይታያል የአፍ ሥዕል የአፍ ግማሽ ሥዕል ሆኖ ታገኘዋለህ። የ ሀ ድምጽ የአፍ መክፈቻ ከውስጥ በእስትንፋስ ገፍተን አፋችንን ስንክፍት ልክ የሀ ድምጽ የአፍ ግማሽ ሥዕል ሆኖ ይገኛል።

ሀሌታው ‘ሀ’  ቤተሰቦች

በዚህ ሳምንት የእናት ፊደል ሀ ንና ቤተሰቦቿን እንጎበኛለን። እንደሚታወቀው የአማርኛ የፊደል ገበታ እናት ፊደላት ጋር አናጋሪ ቅጥሎችን በመጨመር በሰባት መደብ ተባዝተው ድምፅ እንዲሰጡና እንዲጻፉ ተደርጎ የተዋቀረ ነው።ለምሳሌ፦ እናት ፊደል “ሀ” ላይ ጉጦችን ከጎን፥ ከግርጌ፥ እግር በማስረዘም ፥እግር በመቆለፍ፥ አንገት በመቆልመም ድምጽ እንዲያስገኙ በማድረግ አርቢ ፊደሎች ይፈጠራሉ። ይህንንም ከታች በምስል እንመልከተው

ሀሌታው ‘ሀ’  ስንት ቤተሰቦች አሉት?

በመደበኛነት ፮ አርቢ ፊደላት (ሀ ግዕዝ ሲሆን ሁ የ ሀ ፊደል ካእብ ዘር፣ሂ ሳልስ፣ሃ ራብዕ፣ሄ ሀምስ፣ ህ ሳድስ ፣ ሆ ሳብዕ ናቸው።) ቢኖሩንም አሁን የማንጠቀምባቸው ሌሎች ፍንጽቆች(ህፁፃን/ዲቃሎች) ከእናት ፊደላት ላይ አናጋሪ ቅጥሎችን በመጨመር የተፈጠሩ አርቢ ፊዳላትን እርስ በርስ በማዳቀል አርቢ ድርብ ፊደላት ( ድርብ ድምጽ ፊደላት) ተፈጥረዋል።እነዚህም በ ሀ ወገን ቁጥራቸው ፭ ነው። ይህንን ይበልጥ ገላጭ ለማድረግ በተንቀሳቃሽ ምስል እንመልከተው ፦

ይህም በአጠቃላይ የ ሀ ዘር ፊደላትን ወደ ፲፪ ገደማ ያደርሰዋል። እንዲህ አይነት ብዜት አብዛኞቹ ፊደላት ላይም ይታያል። በአማርኛ ቋንቋ ሀ፣ሐ፣ኀ ተመሣሣይ ድምፅ አላቸው።በአማርኛ የፊደል ገበታ የተመሣሣይ ድምፅ ፊደላት (ሞክሼ ፊደላት) አስፈላጊነት እና ፤ ትክክልኛ የተመሣሣይ ፊደላት አገባብና አጠቃቀም በአማርኛ ሥነ-ጽሕፈት ውስጥ ምን መሆን እንዳለበት በቀጣይ በተከታታይ በሥዕላዊ መረጃዎች በሰፊው የምናይ ይሆናል።የሳምንቱን ፊደል እዚህ ላይ አጠናቀቅን መልካም ሳምንት ይሁንልን፣ ሰላም።

እዚህ ልጥፍ ላይ የሚጨምሩት ይዘት አለ? ወይስ የሚያበረክቱት አዲስ ልጥፍ አለ? እንግዲያውስ ይህንን ይጫኑ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

የቴሌግራም ቤተሰብ ይሁኑን
በኢንስታግራም ይከተሉን
የፌስቡክ ገጻችንን ይወዳጁ
ምርጥ የተሸጡ ምርቶች

በማህበራዊ ሚዲያ ያጋሩን

በመረጡት ሚዲያ በማጋራት እንደርስዎ ሌሎችም እንዲያቁን ያድርጉ።

Share on facebook
ፌስቡክ
Share on twitter
ትዊተር
Share on telegram
ቴሌግራም
Share on pinterest
ፒንትረስት

በማህበራዊ ሚዲያ ይከተሉን

© ፳፻፲፪ geezfonts.com