የግዕዝ/አማርኛ መልከ-ፊደላት ያሉት ውስን የፊደል ዓይነቶች ናቸው። እነዚህም ቢሆኑ በትላልቅ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ለሀገሬው ለማዳረስ በሚገባው ቋንቋ ከድርጅቶቻቸው ጋር አብሮ የሚሄዱ ቁምፊዎች(fonts)
localization and internalization ውጤቶች ናቸው። የሚገርመው ባብዛኛው የውጭ ድርጅቶች መሆናቸው ነው። ከነዚህ ባለፈ ስራው እጅግ ፈታኝ ቢሆንም አንዳንድ ለሀገር አሳቢ ብርቅየ ግለሰቦች በራሳቸው ተሰሳሽነትና ወጭ ሰርተው በነፃ ለሀገራቸው የተበረከቱ ናቸው። ሆኖም ግን አሁን ላይ ሁሉም የሚገባቸውን እውቅናና ክብር የተሰጣቸው አይመስልም።
ከዚህ በታች አስር አሪፍና ነፃ የአማርኛ ቁምፊዎች ቀርበዋል።
1.ኢብሪማ
ኢብሪማ የማይክሮሶፍት ሲስተም ፎንት ሲሆን በየትኛውም የዊንዶውስ ምርቶች ላይ ሊያገኙት ይችላሉ።

2.ከፋ
ከፋ የአፕል ሲስተም ፎንት ሲሆን በየትኛውም የማክ ወይም አይፎን ምርቶች ላይ ሊያገኙት ይችላሉ።

3.ኖቶ ሳንስ

ኖቶ የሚለው(No Tofu) የሚለውን ስም ይወክላል። ይህም ከዚህ ቀደም በተለይ ኢንተርኔት ላይ ስንጠቀም አንድንድ ቋንቋዎች አማርኛን ጨምሮ ፊደሎቹን ማሳየት ስለማይችል የስኴር ወይም የሳጥን ምልክት፣ የጥያቄ ምልክት ያሳይ ነበር። እነዚህን ምልክቶች Tofu ይሏቸዋል። ጎግል እነዚህን ለማጥፋትና ሁሉም ቋንቋዎች በኢንተርኔት ላይ መነበብ እንዲችሉ የሰራው ስራ ስለሆነ ሊመሰገን ይገባዋል። ፎንቶቹንም በነፃ ለማንኛውም አገልግሎት መዋል የሚችሉ ዘመናዊ ናቸው። ይህንን ፎንት ከጎግል ፎንቶች በነፃ ማውረድ ይችላሉ።
4.ኖቶ ሴሪፍ

ይህ የኖቶ ሳንስ ሴሪፍ(ጌጠኛ ቅጥያዎች የተጨመሩበት) ቅጂ ሲሆን ይህንንም ፎንት ከጎግል ፎንቶች በነፃ ማውረድ ይችላሉ።
5.ዋሸራ
ዋሸራ 4.0 ሁለት ክፍሎች አሉት፤ እነሱም የኢትዮጵያ ፊደል ፎንቶች (WashRa Fonts) እና የፊደል መምቻ ሥርዓት (keyboard layout) ናቸው። ዋሸራ 4.0 ዐሥራ ሁለት ፎንቶች አሉት። እነዚህ ፎንቶች የዩንኮድን 3.0 ደንብ ያከብራሉ። በተጨማሪ ለተጠቃሚዎች ለልዩ ልዩ ሥራዎች የሚያገለግሉ መልኮችና ቅርጾች ይለግሳሉ። አንባቢው እንደሚታዘበው፥ ከዐሥራ ሁለቱ መካከል ሦስቱ የአይታሊክስ ስታይል አላቸው።

የተሰራው በአቶ አባስ አለምነህ Senamirmir Project ሲሆን በሥነ ምርምር ድረ-ገጽ http://www.senamirmir.com ማውረድ ይቻላል።
6. ዋዜማ

በ አቶ ወሌ፡ነጋ የተሰራ የማስሊያ፡መጻፊያ፡ሥርዐትና ፎንቶችን ያካተተ ሲሆን በድረ ገጹ http://www.gzamargna.net ማውረድ ይቻላል።